- ታሪኩ እንዳጠየቀው - ማነው እየሄደ እየሞተ ያለው?!
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
November 14, 2021
“እኔ የምፅፈው ማንንም ለማስደሰት አይደለም። ማንንም ለማሳዘንም አይደለም። ሙግት ለመፍጠርም አይደለም። ውይይት ለማካሄድ ነው። አተካሮ ለመፍጠር አይደለም። የሰከነ ሀሳብ ማንሸራሸር ቢቻል ብዬ ነው…. በአጭሩ የሰከነ ውይይት ለመፍጠር ነው።”
(ጋሽ አሰፋ ጫቦ - የትዝታ ፈለግ)
አገራችን ወደቀውስ ከመግባቷ በፊት ጀምሮ ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን በፖለቲካዊ ንግግሮችና በሁሉን አሳታፊ ድርድር በመፍታት በኢትዮጵያ ብልጭ ብሎ በርቶ የተዳፈነውን የለውጥ ተስፋ በሙሉ እንዳናመክነው ይልቁንም ወደትክክለኛው መስመር እንዲመለስ በዚሁ ገፅ እና በአገራችን የህትመት ብዙኃን መገናኛዎች በኩል ስናሳስብ ቆይተናል፡፡
አለመታደል ሆኖ ለውጣችን ከህዝብ ሠላምና ከአገራችን ዘላቂ አንድነት ይልቅ በሥልጣን ወዳዶች የእርስ በእርስ ትንቅንቅ እና በዋነኝነትም በኢህአዴጋውያን በኩል እንዲከሽፍ ሆኗል፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ የህወኃት ቡድን ጥቃት ማድረሱን በውድቅት ሌት የነገረን ቢሆንም ይህ ሚስጥር ወደፊት የሚጣራ መሆኑና ታሪክ የሚፈርደው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ “ህግ ማስከበር!” በሚል ስያሜ የተገባበት ዘመቻ ወደእርስ በእርስ ጦርነት ከፍ ካለ እነሆ አንደኛ ዓመቱን ተሻግሯል፡፡
በሸኘነው አንድ ዓ
- ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ሁለተኛው ክፍል)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021
“If history repeats itself and the unexpected always happens, how incapable must Man be of learning from Experience?”
(ጆርጅ በርናንድ ሾው)
ጦርነት እና የነባሩ “ባህላችን” አበርክቶ!
በቀደመው ፅሁፍ የነካካነው የ“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ነባር “ኢትዮጵያዊ” ባህል ከትውልዳችን ዕሴቶች ጋር መቃረኑ፤ ለፖለቲካዊ ጥያቄዎችና ግቦች ብሎም ለሥልጣን መደላድል ሲባልም የጦር ባህልን ዋነኛ መሳሪያው ማድረጉ ሺህ ዓመታትን እንደተሻገረ የተለያዩ የታሪክ ወፖለቲካ ድርሳናት ይነግሩናል፡፡ የኢህአዴግ ሥርዓት አልባና ህግን ያልተከተለ ፍርሰት ጦሱ ለአገራችንም ተርፎ እነሆ ጦርነትን ቀዳሚው ምርጫችን እንዳደረግን በአዝማናት መካከል ቀጥለናል፡፡
ይህን የጦር ባህልን ያለመግራታችን ብዙ እንደሚያስከፍለን ቢታወቅና በዚህ መጣጥፍም ልንነካካው ቀጠሮ ብንይዝለትም ሙዚቀኞቻችንና ግጥሞቻቸው በዚሁ የ“ገዳዬ ገዳዬ…” እና “ኸረ ጎራው!” ይሉት ባህላችን ውስጥ ታሽተው የመጡ በመሆናቸው ይህንን አይነቱን የተሳሳተ አልያም ጊዜ ያለፈበት የአገር ወዳድነትና አርበኝነት (Patriotism) ዕይታ እና
- ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - ሶስት በሉ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
August 5, 2021
“State sovereignty implies responsibility, and the primary responsibility for the protection of its people lies with the state itself. Where a population is suffering serious harm, as a result of internal war, insurgency, repression, or state failure, and the state in question is unwilling or unable to halt or avert it, the principle of non-intervention yields to the international responsibility to protect.”
(Report of the International Commission on Intervention and State Sovereignty, The Responsibility to Protect: Core Principle one)
ሉዓላዊነት የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች እየጣሱ መደበቂያ ሊሆን እንደማይችል ለማሳየት የጀመርነው ህግን ይልቁንም ዓለማቀፉን ህግ መነሾው ያደረገው መጣጥፍ እነሆ ሊያበቃ ሆነ፡፡ በቀደሙት ክፍሎች ከሉዓላዊነት የምንነት ፅንሰ ሃሳብ አንስቶ እስከ የአፍሪካችን ባህርያተ መንግሥታት ድረስ ዘልቋል፡፡ የአህጉራችን መንግሥታት ከጥንት እስከዛሬ የሰው ልጆችን መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች አክብሮ ከማስከበር ይልቅ መ
- ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - አንድ በሉ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
June 18, 2021
“There are two kinds of Injustice: the first is found in those who do an injury; the second in those who fail to protect another from injury when they can.”
(Cicero, a Roman Jurist)
በቀደመውና “ታለ በሉዓላዊነት ስም!” የሚል ርዕስ በሰጠነው መጣጥፍ “ሉዓላዊነት” ምን ማለት እንደሆነና እንዳልሆነ ጭምር በማሳየት የአህጉረ አፍሪካችን ገዢዎች “በሉዓላዊነት ስም” ዜጎቻቸው ላይ እያደረሱት ያለውን ዘርፈ ብዙ በደል ለመመልከትና ዘመኑ እያለፈበት ስለመምጣቱም ተጠቋቁመናል፡፡ የሉዓላዊነትን ተራማጅ ፍቺ መነሻ በማድረግ አገራችንን ጨምሮ ወንበሯን ያገኙ አምባገነን መንግሥታትን ክሽፈት እየነቃቀስን ዛሬም እንቀጥላለን፡፡ በዚህም የ“ዓለማቀፉ ማህበረሰብ” ሚናና የጣልቃ-ገብነቱን ሁኔታ እናወሳሳለን - መልካም ንባብ!
“ሉዓላዊነት” እንደ መብትም - እንደ ግዴታም!
በህገ ፍልስፍናው ዙሪያ ስለ “ሉዓላዊነት” በቀደመው ክፍል ያወሳናቸው ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው ቁጥራቸው ቀላል ተብሎ ሊናናቅ የማይገቡ ሰዎች ገዢው የፖለቲካ ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጉባዔ ሲቀመጥ በድጋሚ ተስፋ
- አንዳንድ ነጥቦች - ስለሰሞንኛው ፖለቲካችን
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
April 1, 2021
የዳያስፖራው ፖለቲካ - እንደግመል ሽንት?!
የኢትዮጵያች ፖለቲካ በብዙዎች እንደተተሰፈው ሳይሆን በጥቂት ሩቅ ተመልካቾች ቀድሞም እንደተፈራው “ከድጡ ወደማጡ” እየገባ ስለመሆኑ በድጋፍም ተቃውሞውም ጎራ የተሰለፉ ወገኖቻችን ልቦና የሚረዳው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለእኩልነትና ነፃነት፤ ለሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለአካታች አገራዊ አንድነት የተደረገውን ትግል በመጥለፍ “የለውጥ ኃይል” ነኝ ብሎ ብቅ ያለውና በኋላ ላይ በኮ/ል ዓብይ አህመድ አሊ የአምባገነንነት ፍላጎትና የንግሥና ምኞተ ፈቃድ ስር ያደረው ኢህአዴጋዊ ስብስብ ከአመራር ክህሎት እጦት ባልተናነሰ በሥልጣን ሽኩቻውና ባደረ የቂም መንገዱ አገራችንን ቁልቁል ይዟት መንደርደር ከጀመረ ሰንብቷል፡፡
አለመታደል ሆኖ ትናንት በዚያ ክፉ የሰቆቃ ዘመን ሽፋን ያልቀየረውን ኢህአዴግ በብርቱ ሲተቹና የተሻለ አገራዊ ፍቅርን ሲያሳዩ የነበሩ ሰዎች፤ ትናንት የበቁ፤ የነቁና ያወቁ ይመስሉ የነበሩ ሰዎች ይልቁንም በምሁሩ አካባቢ የነበሩቱ ጃኬት ቀይሮ የመጣውን ኢህአዴግ ለማገልገልም ሆነ “የንጉሠ ነገሥትነት ቅዠት” ላይ ያለውን መሪ ይሁንታ ለማግኘት መርህ አልባነትን እንደመርህ፤ አቋመ ቢስ መሆንን እንደ አቋም ሲይዙ መመልከቱ በዝቷልና በርካቶች ወደቀደመ ዝምታቸው እንዲመለሱ ሆነዋል፡፡ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙና መሀንዲሱ ሳሙዔ
- ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!! (ወግ መቋጫ ሶስት - ስላቀ ምግብ ወልባስ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
February 4, 2021
“ሀብታሞች ለስጋቸው ሆድ ሲፈልጉ
ድሆች ደግሞ ለሆዳቸው ስጋ ይፈልጋሉ!”
(የሕይወት ተቃርኖ)
“ሱፉን ግጥም አርጎ ተከርክሞ ፀጉሩን
መልዓክ መስሎ ታየኝ ወይ ያለው ማማሩ!”
(አስቴር አወቀ - በህዝብኛ)
አገርህ በንዋዩ በኩል ባትታደልም የበዓላት ሀብታም ነችና በቀደመው ፅሁፌ በተሳልቆ ውኃ ከነቋቆርኩህ በኋላ ተጣፍተን ከረምን፡፡ እንደምን አለህልኝ ወዳጄ ልቤ?! በዓላትን መለዮዋ ባደረገች ቺስታ አገር ላይ በዓሉስ እንዴት አለፈልህ ይሆን?! ያው የገናን ቅንጥብጣቢ ለጥምቀት ከሚያሻግሩት እንጂ ጥምቀትንም ራሱን የቻለ በዓል ከሚያደርጉት ወገን አይደለህም ብዬ ነው…. አልሞላ ያለ ኑሮህስ እንዴት ይዞሃል…?! ለነገሩ የድኃ ነገር ሆኖ ጠግባችሁ የበላችሁና ከርሳችሁ የሞላ ቀን የዓመት ርኃባችሁን ትረሳላችሁና አይዞን! “ያልተፈተነ አያልፍም!” ነው ነገሩ፡፡
በቀደመው ክፍል “ድኃ አይጣላ ከውኃ!” ይሉትን በተሟላ መልዕክት ስር ያልተሟላ ሆኖ የቀረበልንን የሙዚቃ ግጥም ስናነሳሳ በድምፅም በቀልድና ጨዋታውም አይጠገቤ ከመሆኑም በላይ ድህነቱና ድህነታችን ላይ “እህ!” በሚያስብል ግራሜ ሳቅ ይፈጥርልን የነበረውን የካሳ ልጅ ተስፋዬን ከቻርሊ ቻፕሊን ጋር አማስለን አውስተነውም አልነበር?! ሌላ “ድ
- ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
(ወግ መቋጫ ሁለት - ስላቀ ኑሮ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
January 11, 2021
“I am neither an Optimist nor a Pessimist. But a Possibilist.”
(Hans Rosling)
አገርህ እንዲህ እንደዛሬው የጠቢብ እጥረት ሳያጋጥማት በፊት እንደሳቅ ንጉሡ ቻርሊ ቻፕሊን ሁሉ ድህነቱንና ድህነትህን በምሬት ሳቅ የሚያዋዛልህ ተስፋዬ ካሳ የሚባል ሰው ነበረ… ይህ ቀልዱ ብቻ ሳይሆን ድምፁም ያማረለት ሰው በአንድ የበዓል ጨዋታው ላይ ህፃን ልጅ “እማዬ ፆም ሲፈታ….?!” ብሎ ድኃ እናቱን ይጠይቅና የእናትዬውን ምላሽም ያቀብለናል፡-
“ልጄ! ፆም ሲፈታማ ሌላ ፆም እንይዛለና!”
እነሆ…. አንተም ዕድለ ቢሱ ወዳጄ ፆም ተፈታልህና ሌላ ፆም ይዘሃል... በቀደሙት ክፍሎች ይልቁንም ድህነትን ከፍቅርና ጦርነት ጋር እያሰናሰልን በተሳለቅንበት ክፍል የሀዲስ ዓለማየሁን “ፍቅር እስከ መቃብር” ዋቢ አድርጌ የበዛብህን ድህነት የተጫነው ብሶት አስመልክቼህም አልነበር?! አዎ! ብዙ ተመልካችና አጀብ ያላትን ሴት ልብህ እንዳይከጅል በአሸናፊ ከበደ “አንቺን የብቻዬ ቢያደርግልኝ… አይ ዕድሌ!” እንጉርጉሮ በኩል ተግሳፄን